አባልበመሆንዎየሚያገኙትጥቅም፡-
- አባላት በዘርፉ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡ላኪዎች ለኤክስፖርት ስራቸው የሚያግዙ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሁኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ስልጠናዎቸ ይሰጣሉ፡፡
- አባላቱ በኤክስፖር ንግድ ስራቸው የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከሚመለከታቸው የመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ችግራቸው እንዲፈታ ይደረጋል፡፡
- የኤክስፖርት ንግዱ ቀልጣፋ፣የተሻሻለ እና አዋጭ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እንሰራለን፡፡
- በኤክስፖርት ዘርፉ ያሉ መረጃዎች ለአባላት እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡
- የአለም የገበያ ዋጋ መረጃ በየጊዜው ለአባላት እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡
- የግዥ ፍላጎት ሲቀርብ ለአባላት በማሳዎቅ አባላት ከገዥዎች ጋር ተነጋግረው ምርታቸውን እንዲሸጡ ይደረጋል፡፡
- በሀገሪቱ ዉስጥ የሚመረቱ የሰሊጥና የጥረጥሬ ምርቶችን የምርት መጠን ትንበያ ለአባላቱ እንዲያዉቁት በማድረግ ላኪዎች የምርት አቅም ያላቸውን አካባቢዎች እንዲያዉቁ ይደረጋል፡፡
- አባላቱ የንግድ ክህሎታቸውን ለማሳድግ ይረዳቸው ዘንድ በአለምዓቀፍና በሐገርአቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የንግድ ኤግዚቪሽን፣ የንግድ ትርኢት፣ ኮንፈረንስ፣ የንግድ አቻ ለአቻ ዉይይት፣ወርክሾፕ፣ የንግድ ጉብኝት…ወ.ዘ.ተ እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡
አባልለመሆንየሚያስፈልጉነገሮች፡-
- የንግድ ስራ ፈቃድ
- የንግድ ዋና ምዝገባ
- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር
አባልለመሆንየሚጠየቁክፍያዎች፡-
- የአባልነት መመዝገቢያ - 40000.00 (አርባ ሺህ ብር)
- የአባልነት አመታዊ መዋጮ - 15000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
የክፍያመንገዶች፡-
- በካሽ/በቼክ
- ህብረት ባንክ ሂሳብ ቁጥር - 1131816050760016 ወይም ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር - 1000001847876
የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) – 00004253407
ስልክ - 0116623545/0118699588፣ Mobile +251910300032
ፋክስ - 011662 3504፣
ፖ.ሳ.ቁ - 8686 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ኢ-ሜይል - epospea@gmail.com, epospead@gmail.com,
ድህረገፅ - www.epospeaeth.org